NEWS

In Loving Memory Of Trihas Mezgebe 1953 -2014 EC

ወይዘሪት ትርሃስ መዝገበ በ 1953 ዓም ከእናታቸው ከወ/ሮ ፀጋ ሰበሆ እና ከአባታቸው ከአቶ መዝገበ ገ/መድህን በአስመራ ከተማ ተወለዱ:: ለቤተሰቦቻቸው 5 ልጅ ሲሆኑ ሰባት እህትና አንድ ወንድም ነበራቸው፡፡

Tirhas Mezgebe Memorial Ceremony

በ1979 ዓ.ም በአስመራ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን ቤንሻንጉል ጉሙዝ ፓዌ ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ውስጥ አስተዳዳሪና ገንዘብ ተቀባይ በመሆን ተቀጠሩ፡፡ እዚያም የማታ ማታ የነፍሳቸውን ጥሪ አገኙ፡፡ የደርግ መንግስት ከተገረሰሰና ሳሊኒ ከአከባቢያቸው ከወጣ በኃላ ከስፍራው እንዲለቁ ቤተሰባቸው ግፊት ቢያደርግባቸውም የጉሙዝ ሴቶች ጉዳይ ያስጨንቃንቃቸውና ያሳስባቸው ስለነበር እዚያው ለመቆየት ወሰኑ፡፡ በ1985 አንዲትን ልጅ በጉዲፈቻ ወስደው አሳደጉ፡፡ ከአንድ ዓመት በኃላም ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት ሲወስኑ የህይታቸውን ራዕይ ግልፅ የሚያደርግ አጋጣሚ ተፈጠረ፡፡ በጫካ ወደተከበበችውና በጣት የሚቆጠር ነዋሪ ባለባት ግልገል በለስ በምትባል ትንሽ መንደር ለአንድ ዓመት ያህል በየሳምንቱ በመንደር ውስጥ ካሉ ሴቶች ጋር መቀራረብና መነጋገር ጀመሩ፡፡ በማህበረሰቡ ጋር በነበራቸው ቅርርብ ትምህርት ቤት እንዲከፈትላቸው ጠየቋቸው፡፡ ሁለት ትምህርት ቤቶችን በመክፈትና አስተማሪዎችን በመቅጠር እንዲሁም ለህብረተሰብ ውስጥ ወፍጮ ቤት መክፈት ችለዋል፡፡

Tirhas Mezgebeyራዕያቸውም አነድም እናት በወሊድ ምክንያት አትሙት በሚል መርህ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ጫካ ውስጥ የሚወልዱ ሴቶች ወደ ቤትና ሆስፒታል ውስጥ እንዲወልዱ ሲሆን ይህንንም ለማሳካት ስር የሰደደ ጎጂ ልማዳቸውን ለመቀየር ሳያቋርጡና ሳይደክሙ ሙሉ ህይወታቸውና ጊዜያቸውን መስዋዕት በማድረግ ህይወታቸው እስከሚያልፍበት ሰዓት ድረስ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ በ1996ዓ.ም ከፌደራል የመንግስት በጎ አድራጎት ድርጅት ፍቃድ በማውጣት ምዠዠጓ ሎካ የሴቶች ልማት ማህበርን በመስራችነትና በዋና ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ ይህም ድርጅት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች ላይ እየሰራ ሲሆን 9 ትምህርት ቤቶችን ከተለያዩ ለጋሽ ድርጅች ባገኙት ድጋፍ ገንብቷል፡፡ ከ 30 በላይ የሴቶች ራስ አገዝ ማህበራትን መስርቷል፤ የሴቶች መጠለያና የመረጃ ቴከኖሎጂ ማዕከልን ገንብተዋል፤ የፊስቱላና የማህፀን መውጣት ችግር የደረሰባቸውን ሴቶችን የህክምና የኢኮኖሚ ድጋፍ ከመርዳትም ባሻገር በሴት ልጅ ላይ የሚደርስ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እና ፆታዊ ጥቃቶችን ለማስቆም ከፍተኛ ስራ ሰጥተዋል ፤ ለሴቶች ኢኮኖሚ እድገትና በመብታቸው ዙሪያ ትምህርት ሰጥተዋል ፤ ሴቶች የመሬት ባለቤት በመሆን እርሻ ማረስ እንዲጀምሩ በማድረግ ብዙዎችን አበልፅገዋል፤ ለብዙ ህፃናት የትምርት ዕድልን ፈጥረዋል፡፡ በክልሉ ሴቶች በጫካ ውስጥ ከመውለድ ተገላግለው ቤታቸውና በጤና ማዕከላት መውለድ ችለዋል፡፡ እድሜ ዘመናቸውን ለሴቶች መብት በመታገል ሴቶች የደረሰባቸውን ችግሮችና ተግዳሮቶች አልፈው ራሳቸውን እንዲያበቁ እንዲያበለፅጉ የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ህይወታቸውን መስዋዕት አድርገዋል፡፡

ላበረከቱት ትልቅ አስተዋጽኦ ከAWIB 2007 ዓ.ም፣ የበጎ ሰው ሽለማት 2010 ዓ.ም የእናት ባንክ ቄራ ቅርንጫፍ በስማቸው ተሰይሞላቸዋል እንዲሁም ሌሎችንም ከተለያዩ አካላት ተቀብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት መስራችና አባል ሲሆኑ የተለያዩ ድርጅቶች ቦርድ አባል በመሆን ሲያገለግሉ ቆየተዋል፡፡ ከዚህ በኃላ የነበራቸው ህልም የሴቶችና የህፃናት ሆስፒታል መገንባት ነበር፡፡

CALL US

Need Help?

Feel free to call us and get support!

Contact Us

2023 ©  MUJEJEGUWA LOKA WOMEN DEVELOPMENT ASSOCIATION​  | Developed By Peak Internet & Networking Technologies